#እነሆ_የአቃቂ_ድል_ዜና_ተደገመ! #እንኳን ደስ አላችሁ! የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በ2017 በጀት አመት አጠቃላይ አፈፃፀም ተመዝና በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 11 ክ/ከተማ ም/ቤቶች መካከል 3ኛ ደረጃ በመዉጡት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ። የክ/ከተማዉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙልጌታ አሰፋ ይህ ዉጤት እንዲመጣ የበኩላቸዉን አስተዋፅዖ ላበረከቱ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የምክር ቤት አመራሮች እና አባላት፣ ባለሙያዎች እና የዋሪዎች በራሳቸዉና በተቋሙ ስም በማመስገን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። "አልቆ ለመፈፀም ከህዝብ የተሰጠን አደራ!" ሐምሌ/26/2017 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ